የአያት አክሲዮን ማኅበር ተከሳሾች የተከሳሽነት ቃል ተሰምቶ ተጠናቀቀ
በታምሩ ጽጌ
የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዓቃቤ ሕግ በመሰረተባቸው ክሶች የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 8ኛ ወንጀል ችሎት እንዲከላከሉ ብይን ያስተላለፈባቸው የአያት አክሲዮን ማኅበር፣ አቶ አያሌው ተሰማ፣ አቶ ጌታቸው አጎናፍርና ዶ/ር መሐሪ መኮንን ሲሆኑ፤ የመከላከያ ምስክሮቻቸውን ከማሰማታቸው በፊት ማቅረብ የነበረባቸውን የተከሳሽነት ቃል የአክሲዮን ማኅበሩ የፋይናንስና ኢንቨስትመንት ዳይሬክተር ዶ/ር መሐሪ መኮንን ባለፈው ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ ባሰሙት የተከሳሽነት ቃል ተጠናቋል፡፡