አስተዳደሩ ለኪስ ቦታዎች፣ ለመንግሥት ቤቶችና ለመኖሪያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበራት አዲስ መመሪያ አወጣ

– መሬት አጥሮና ቆፍሮ መጥፋት ዕርምጃ ያስወስዳል

በታምሩ ጽጌ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማው 30 ሜትር ስፋት ባላቸው ዋና ዋና መንገዶች ላይ ለሚገኙ የኪስ ቦታዎች፣ የፌዴራል መንግሥት ለሚያስተዳድራቸው የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ንብረት ለሆኑ ቤቶችና የመኖሪያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበራትን የሚመለከት አዲስ መመሪያ አውጥቶ ተግባራዊ ማድረጉን አስታወቀ፡፡