መንግሥት በፔትሮናስ የተያዙ የነዳጅ ይዞታዎችን ተረከበ

– የጋዝ ክምችቱን በፍጥነት ለመጠቀም ታስቧል

በቃለየሱስ በቀለ

የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያየ ጊዜ ለማሌዥያው የፔትሮሊየም ኩባንያ ፔትሮናስ የሰጣቸውን የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት የሚገኙባቸውን የካሉብና የሂላላ መሬቶችና ሌሎች በኦጋዴን ክልል የሚገኙ የነዳጅ ፍለጋ ቦታዎችን መልሶ ተረከበ፡፡