በአራዳ ክፍለ ከተማ ‹‹ኪራይ ሰብሳቢነት ተንሰራፍቷል›› በሚል ሹማምንቱ በከፍተኛ ግምገማ ተጠምደዋል
– በ12 ቀናት ግምገማ ከ10 በላይ ኃላፊዎች ተነስተዋል
– በክፍለ ከተማው የ10.8 ሚሊዮን ብር ሕገወጥ ግዢ ተፈጽሟል
በታምሩ ጽጌ
– በክፍለ ከተማው የ10.8 ሚሊዮን ብር ሕገወጥ ግዢ ተፈጽሟል
በታምሩ ጽጌ
ኪራይ ሰብሳቢነት በከፍተኛ ሁኔታ በመንሠራፋቱ ልማትን ማፋጠን አለመቻሉን በማመንና ለዚህም ተጠያቂዎቹ ክፍለ ከተማውን በመምራት ላይ ያሉት ሥራ አስፈጻሚዎች መሆናቸው ስለታመነበት፣ በአራዳ ክፍለ ከተማ ያሉ 20 ሥራ አስፈጻሚዎችና አምስት የኮር አባላት ከታኅሣሥ 11 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ በማዘጋጃ ቤትና በአዲስ አበባ የኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት በከፍተኛ ግምገማ ላይ እንደሚገኙ ምንጮች ለሪፖርተር አስታወቁ፡፡