የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ባለሥልጣናት ቤተሰቦች ለደርግ ባለሥልጣናት ይቅርታ እንደማያደርጉ አስታወቁ

በዘካሪያስ ስንታየሁ

በደርግ ባለሥልጣናት የተገደሉት ስድሳዎቹ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ባለሥልጣናት ቤተሰቦች፣ ለደርግ መንግሥት ባለሥልጣናት ይቅርታ እንደማያደርጉ ባለፈው ሐሙስ ባወጡት መግለጫ ለአቡነ ጳውሎስ አስታወቁ፡፡