አቡነ ጳውሎስ የ60ዎቹን የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ባለሥልጣናት ቤተሰቦች ዛሬ ያነጋግራሉ

በዘካሪያስ ስንታየሁ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ በደርግ የተገደሉትን የስድሳዎቹን የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከፍተኛ ወታደራዊና የሲቪል ባለሥልጣናት ቤተሰቦችን ዛሬ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ያነጋግራሉ፡፡