በአዲስ አበባ የሚሠሩ መንገዶችና ኮንዶሚኒየሞች የፋይናንስና የግብዓት ችግር ገጥሞአቸዋል

(በታምሩ ጽጌ)

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንገዶች ባለሥልጣንና የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽ/ቤት የሚያስገነቧቸው ፕሮጀክቶች፣ በተያዘላቸው ዕቅድና ጊዜ ለመጨረስ የማይችሉበት ከፍተኛ የፋይናንስ፣ የሲሚንቶና የግብዓት እጥረት እንዳለባቸው ተቋራጮቹ ገለጹ፡፡