የወጪ ንግድ የሦስት ወራት አፈጻጸም ከዕቅድ በታች ሆኗል

(በውድነህ ዘነበ)

መንግሥት በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት ከወጪ ንግድ 653.4 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ቢያቅድም፣ ማሳካት የቻለው የዕቅዱን 86 በመቶ ወይም 563.4 ሚሊዮን ዶላር ብቻ መሆኑን የንግድ ሚኒስቴር ሪፖርት ያወጣው መረጃ ያመላክታል፡፡