የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ታዘዘ

(በታምሩ ጽጌ)

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ከአራት ወራት በፊት በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጠርጣሪዎች ላይ የተላለፈን ትዕዛዝ ሳይፈጽም በመገኘቱ፣ ጥቅምት 30 ቀን 2003 ዓ.ም. በፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ቀርቦ እንዲያስረዳ ትዕዛዝ ተላለፈ፡፡