የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አቤቱታ ምላሽ አገኘ
– ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ ላይ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጦ ማሻሻያ አደረገ
(በምሕረት ሞገስ)
የትምህርት ሚኒስቴር ነሐሴ 20 ቀን 2002 ዓ.ም. የትምህርት ሥልጠና፣ ጥራትና አግባብነትን ለማረጋገጥ እንቅስቃሴዎች ቢያደርግም፣ ከሚፈለገው ደረጃ አለመድረሱን በመጥቀስ አውጥቶት በነበረው የአፈጻጸም ሥርዓት ላይ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጦ ማሻሻያ አደረገ፡፡