ኦብነግ ከ18 ዓመታት የትጥቅ ትግል በኋላ ከመንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት አደረገ
ትናንት ከቀትር በኋላ በኢትዮጵያ መንግሥትና ለ18 ዓመታት የትጥቅ ትግል ሲያካሂድ በቆየው የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) መካከል በሸራተን አዲስ የሰላም ስምምነት ፊርማ የማኖር ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል፡፡በኢትዮጵያ በኩል ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር፣ በኦብነግ በኩል የድርጅቱ ሊቀመንበር ኢንጂነር ሳላሕዲን አብዱራማን ማኦ የሰላም ስምምነቱን ፈርመዋል፡፡ በስምምነቱ መሠረት ከዚህ በፊት ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ የኦብነግ ታጣቂቶች ተጠያቂ አይሆኑም፡፡ ሁሉም የኦብነግ እስረኞች ከእስር ቤቱ እንዲለቀቁ ይደረጋል፡፡ ዝርዝሩን እዚህ ይመልከቱ