በሊዝ የተሸጡ ቦታዎች ለአልሚዎቹ የሚሰጡበት ቀን መወሰኑ ታወቀ
– የሰንጋተራ ነጋዴዎች በሰባት ቀናት ውስጥ ልቀቁ መባላቸውን ተቃወሙ
(በታምሩ ጽጌ)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለተለያዩ አክሲዮን ማኅበራት በሊዝ የተሸጡ ቦታዎችን የክፍለ ከተማ አስተዳደሮች እስከ መስከረም 30 ቀን 2003 ዓ.ም. ድረስ አጠናቀው ማስከረብ እንዳለባቸው ጥብቅ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡