የኮንስትራክሽን ዘርፉ በትራክተር የሚጎተቱ መለስተኛ መሣሪያዎችን እንዲጠቀም ዕቅድ ተይዟል
– አቅራቢዎችና ኮንትራክተሮች ዋጋ ለማረጋጋት ተስማሙ
(በዳዊት ታዬ)
የኮንስትራክሽን ዘርፉ በቀጣይ ዓመታት ትልልቅ መሣሪያዎችን ከመጠቀም ይልቅ፣ መካከለኛና መለስተኛ በትራክተር ኃይል የሚጎተቱ መሣሪያዎች እንዲጠቀም መታሰቡ የዕድገትና የትራንስፎርሜሽኑ ዕቅድ አንድ አካል እንደሆነ፣ የሥራና የከተማ ልማት ሚኒስትሩ አስታወቁ፡፡