የግብዣ አዳራሹ ወደ ቢሮነት መለወጡ እያነጋገረ ነው

(በውድነህ ዘነበ)

ላለፉት አሥርት ዓመታት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንግዶቿን ስትጋብዝ የቆየችበት የግብዣ አዳራሽ፣ የመሬት አስተዳደርና ግንባታ ፈቃድ ባለሥልጣን ቢሮ አድርጐ እንዲጠቀምበት ተሰጠው፡፡ አዳራሹ ለቢሮዎች በመሸንሸኑ የአዲስ አበባ አስተዳደር ሠራተኞች ቅሬታ አድሮባቸዋል፡፡