የሸራተን አካባቢ ተነሺዎች የምሬት አቤቱታቸውን አቀረቡ

(በውድነህ ዘነበ)

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተስፋ የቆረጡት የሸራተን አዲስ ሆቴል ማስፋፊያ ተነሺዎች ትናንት ማክሰኞ ጥቅምት 9 ቀን 2003 ዓ.ም. በሸራተን ሆቴል በር ላይ በመሰባሰብ ሼክ መሐመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ አንዳች መፍትሔ እንዲሰጧቸው ምሬት የተቀላቀለበት ተማጽኖ አቀረቡ፡፡