የደኢሕዴን ጉባዔ መተካካት አጀንዳው አልነበረም

– አቶ ብርሃኑ አዴሎ ለማዕከላዊም ሆነ ለሥራ አስፈጻሚነት አልተመረጡም

(በታምሩ ጽጌ)

የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) በሐዋሳ ከተማ ከመስከረም 2 እስከ 4 ቀን 2003 ዓ.ም. ባካሄደው 7ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ መተካካትን በሚመለከት አጀንዳው እንዳልነበረ አስታወቀ፡፡