አራት የፖለቲካ ፓርቲዎች በአንቀጽ 39 እና በመሬት ጉዳይ ሳይስማሙ ጥምረት ፈጠሩ

(በታምሩ ጽጌ)

የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ንቅናቄ (ኢዴአን)፣ መላው የኦሮሞ ሕብረት ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (መኦሕዴፓ)፣ የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኦብኮ) እና የመላው ኢትዮጵያ ብሔራዊ ንቅናቄ (መኢብን) በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 39 እና በመሬት ባለቤትነት ጉዳይ ሳይስማሙ ከነልዩነቶቻቸው (40 በመቶ) ጥምረት መፍጠራቸውን ጳጉሜ 1 ቀን 2002 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ አስታወቁ፡፡