የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ትምህርት ሚኒስቴር ሊስማሙ አልቻሉም

– ተቋማቱ ከቴክኒክና ሙያ ወደ ፖሊ ቴክኒክ እንዲሸጋገሩ ተነገራቸው

(በምሕረት ሞገስ)

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማኅበር አዲስ የወጣውና ተቋማቱን የርቀት፣ የሕግና የመምህራን ትምህርት ከመስጠት የሚገድበው አዲስ ሥርዓት አግባብ አይደለም ሲል ለትምህርት ሚኒስቴር ባቀረበው አቤቱታ ላይ፣ ከሚኒስቴሩ ጋር ቢወያዩም ሊስማሙ አልቻሉም፡፡