ኦብኮ፣ መኢብን፣ ኢዴአንና መኦህዴፓ ጥምረት ለመፍጠር ተስማሙ
– የመተዳደሪያና የሥነ ምግባር ደንብ አርቅቀዋል
(በታምሩ ጽጌ)
የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኦብኮ)፣ የመላው ኢትዮጵያውያን ብሔራዊ ንቅናቄ (መኢብን)፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ንቅናቄ (ኢዴአን) እና የመላው ኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (መኦህዴፓ) ከነሐሴ 25 ቀን 2002 ዓ.ም. ጀምሮ በጥምረት ለመንቀሳቀስ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ለሪፖርተር ገለጹ፡፡