በሊቢያ ለስምንት ዓመታት በግፍ ታስረን ነበር ያሉ ዜጐች መብታችን ይከበር እያሉ ነው

(በትዕግሥት ዘሪሁን)

ምንም ዓይነት ወንጀል ሳይፈፅሙ ‹‹የሲአይኤ ሰላይ ናችሁ፤ ፈላሾች ናችሁ፤›› በሚል ለስምንት ዓመታት ያህል ያለክስና ያለፍርድ በሊቢያ መንግሥት ታስረው የቆዩ ኢትዮጵያውያን፣ በመንግሥት ትብብር ከ10 ዓመት በፊት ወደ አገራቸው ቢመለሱም፣ እስካሁን ድረስ በኤግዚቢትነት የተያዘ ንብረታቸው አለመመለሱን፣ በይፋ ይቅርታ እንዳልተጠየቁና ያለፍርድ ለታሰሩባቸው ዓመታትም ካሳ እንዳልተሰጣቸው በመግለጽ መንግሥት ‹‹የዜግነት መብታችን አላስከበረልንም፤›› ሲሉ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡