የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የወጣው መመሪያ ተቃውሞ ገጠመው
– የመንግሥትም ሆነ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በቅድመና በድኅረ ምረቃ የርቀት ትምህርት አይሰጡም
– የሕግና የመምህራን ትምህርት በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መሰጠት ይቆማል
– ‹‹ሥርዓቱ ሙሉ ለሙሉ የትምህርቱን ዘርፍ የሚገድብ ነው›› ረዳት ፕሮፌሰር ወንድወሰን ታምራት
– ‹‹ግብታዊ ውሳኔ ነው፤ የአቤቱታ ደብዳቤ እናስገባለን›› ዶ/ር ነጋ ነማጋ
በየደረጃው የትምህርት ጥራትና አግባብነትን ለማስጠበቅ፣ በግልና በመንግሥት የትምህርትና ሥልጠና አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት የትምህርት ሚኒስቴር የማስተካከያ ዕርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡