የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ፈተናዎችና ገመናዎች

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የፈሰሰበት፣ ከግብርናው ዘርፍ ቀጥሎ በርካታ የሰው ኃይል የተሰማራበትና በአገሪቱ ውስጥ ካሉ ሌሎች የኢኮኖሚው ዘርፎች ከፍተኛ ትኩረትን የሳበ ነው፡፡ ዘርፉ በአገሪቱ የመሠረተ ልማት እንቅስቃሴዎች ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ የሚገኝ ቢሆንም በበርካታ ችግሮች የተተበተበ ነው፡፡ ቀጣዩ ልዩ ዘገባ የኮንስትራክሽን ዘርፉን ገጽታ ያሳየናል፡፡