የካናዳው ኩባንያ በኦሞ ሸለቆ የነዳጅ ፍለጋ ቦታ ተረከበ

– በአካባቢው ጥናት ለማካሄድ 6.5 ሚሊዮን ዶላር መድቧል

(በቃለየሱስ በቀለ)

አፍሪካ ኦይል የተሰኘ ተቀማጭነቱ በቫንኮቨር ካናዳ የሆነ የነዳጅ ኩባንያ፣ በደቡብ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ኦሞ ሸለቆ የነዳጅ ፍለጋ ሥራ የሚያካሂድበትን መሬት መረከቡን አስታወቀ፡፡