አራጣ አበዳሪው ገብረ ኪዳን በየነ (ሞሮኮ) የ21 ዓመት ጽኑ እሥራት ተፈረደባቸው

– 211 ሺሕ 200 ብር የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባቸዋል

(በታምሩ ጽጌ)

የኢትየጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዓቃቤ ሕግ በ2001 ዓ.ም. መጨረሻ አካባቢ ክስ የመሠረተባቸው አራጣ አበዳሪው አቶ ገብረ ኪዳን በየነ (ሞሮኮ)፣ በ21 ዓመት ጽኑ እሥራትና የ211 ሺሕ 200 ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ ተወሰነባቸው፡፡