የጣና ወርቅ ቤትን የዘረፉ ተከሳሾች ጥፋተኛ ተባሉ
– ከሦስት ሚሊዮን ብር የሚበልጥ ወርቅና ንብረት ዘርፈዋል
(በታምሩ ጽጌ)
የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ሚያዚያ 18 ቀን 2001 ዓ.ም. በአራዳ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 10 ውስጥ ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው ጣና ወርቅ ቤት ላይ ዝርፊያ አካሂደዋል በሚል ጥር 7 ቀን 2002 ዓ.ም. ክስ ከመሠረተባቸው ሰባት ተከሳሾች መካከል ስድስቱ ጥፋተኛ ተባሉ፡፡