በ14 ፓርቲዎች ሊመሠረት የታቀደው ግንባር ሳይሳካ ቀረ

(በኃይሌ ሙሉ)

በቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አየለ ጫሚሶ አስተባባሪነት በአሥራ አራት ፓርቲዎች ሊመሠረት ታስቦ የነበረው ግንባር ሳይሳካ ቀረ፡፡ አብዛኛዎቹ ፓርቲዎች ራሳቸውን ከድርድሩ አግልለዋል፡፡