ለታራሚዎች ይቅርታ ሲደረግ መስፈርቶቹ ወጥ መሆን አለባቸው ተባለ

– የይቅርታ አሰጣጥና አፈጻጸም ሥነ ሥርዓት አዋጅ ረቂቅ ቀረበ

(በታምሩ ጽጌ)

በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ተፈርዶባቸው በፌዴራልም ሆነ በዘጠኙም ክልሎች ውስጥ በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ታራሚዎች ይቅርታ ሲደረግላቸው፣ የይቅርታ መስፈርቶቹ መለያየት እንደማይገባቸውና ወጥነት እንዲኖራቸው ተጠየቀ፡፡