ከ7000 በላይ የቦንጋ ነዋሪዎች በአቶ ብርሃኑ አዴሎ ላይ ያላቸውን አቤቱታ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ላኩ

– ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ እንዲያነጋግሯቸው ጥሪ አቅርበዋል

(በጋዜጣው ሪፖርተር)

በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፣ በካፋ ዞን የቦንጋ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ከ7000 በላይ ሰዎች፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በአቶ ብርሃኑ አዴሎ የደረሰባቸውን በደልና የመልካም አስተዳደር እጦት የሚያስረዳ አቤቱታ ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባሳለፍነው ሳምንት መላካቸውን አስታወቁ፡፡