መከላከያ ኮንስትራክሽን የሁለት ቢሊዮን ብር የመንገድ ግንባታ ሥራ ተሰጠው
– ሦስት ኮንትራክተሮች ለመጀመሪያ ጊዜ የፌዴራል መንገድ ሥራ ተረከቡ
(በዳዊት ታዬ)
የተለያዩ የመከላከያ ፕሮጀክቶችን ብቻ በመሥራት የሚታወቀው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ፣ ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ሁለት ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ወጪ የሚጠይቁ የመንገድ ግንባታዎችን ተረከበ፡፡ ሦስት የግል ኮንትራክተሮች ለመጀመሪያ ጊዜ በፌዴራል የመንገድ ግንባታ ውስጥ ገቡ፡፡