የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ድርጅትን ለመርዳት 27ሺህ ዶላር ተሰበሰበ
Ethiopia Zare (ሰኞ ግንቦት 8 ቀን 2003 ዓ.ም. May 16, 2011)፦ የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ማህበርን ለመርዳት ከተለያዩ የአሜሪካና ካናዳ ግዛቶች የተሰባሰቡበት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ከ27ሺህ የአሜሪካ ዶላር በላይ መሰብሰቡ ተገለጸ። በርካታ ኢትዮጵያዊያንና ተጋባዥ ተናጋሪዎችም በስፍራው ተገኝተው ለማህበሩ ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል።