ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ
“ቤን አሊን ተመልከቱ፣ ሙባረክን ወይንም ጋዳፊን ስሟቸው ሁሉም ህዝባዊ ጥያቄ ሲበረታባቸው የሰጡት መልስ ተመሳሳይ ነው። ‘እኔ ስልጣኔን ብልቅ ሀገሪቱ ቀውስ ውስጥ ትገባለች የእርስ በርስ ጦርነትም ይከሰታል።’ ነበር ያሉት ይህ የተበላበት ክርክር ሲሆን የሚያሳዝነው ግን የምእራቡ አለም መሪዎች በተወሰነ ደረጃ ሊቀበሉት የመፈለግ አዝማሚያ የሚያሳዩ መሆናቸው ነው። “ይህ ወቅት በተግባር ያረጋገጠው ነገር ሌላው ቀርቶ የተቃዋሚ ፓርቲ ሳይኖር እንኳን ህዝብ ነጻነቱን ካገኘ ወደ እርስ በርስ ጦርነት የማያመራ መሆኑን ነው። ህዝቡ ነጻነት የሚመጣው ከሀላፊነት ጋር መሆኑን ጠንቅቆ ይገነዘባል።