በካናዳዋ መናገሻ ኦታዋ ለኢሳት ገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ተጧጡፏል
Ethiopia zare (ሐሙስ ሚያዝያ 13 ቀን 2003 ዓ.ም April 21, 2011)፦ በካናዳ ዋና ከተማ ኦታዋ በያዝንው ወር ቅዳሜ ሚያዚያ 30 ቀን ለኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን ማጠናከሪያ የሚሆን የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ አርቲስት ታማኝ በየነና የተለያዩ የካናዳ የፖለቲካ ሰዎች በተገኙበት እንደሚካሄድ ተገለጸ።