ሕዝባዊ የሙዚቃ ጥበብ ባለሙያዎች!

 ፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማሪያም

“ሙዚቃ የአለም ቋንቋ ነው ተብሏል”። ጥቂት የሙዚቃ ኖታዎችን በማንሳትና አነስ ያለ የግጥም ዘለላ በመጻፍ የሙዚቃ ደራሲዎችና ድምጻዊያን በጨቋኝ መሪዎች፣ በአምባገነን ገዥዎች፣ ጸረ ዲሞክራሲያዊና ኢ-ፍትሀዊ በሆኑ ወገኖች ላይ ጥበባዊ ጦርነት አካሂደዋል። ሙዚቃ ከድንጋይ የተሰራውን የጥላቻ ግድግዳ በርቅሶ በማለፍ፤ ህሊናን የዘነጋን ስብእና የመንፈስ ጭለማዊ ጥቀርሻ ለመግፈፍ ቅዱስ ቋንቋ ሆኖ ታይቷል። ተደምጧል።