ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አመጽ ሊያስነሱ እንደሚችሉ ተነበየ
በእረፍት ላይ የሰነበቱት ተማሪዎች ወደግቢ እየተመለሱ ነው
ጠንካራ ፖለቲካዊ ጽሁፎችን በመጻፍና ድፍረት የተሞላባቸውን ሀሳቦች በማስተጋባት የሚታወቀው፡ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፡ ከእረፍት እየተመለሱ ያሉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እንደ ግብጽና ቱኒዚያ አጋሮቻቸው የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ሁኔታ ሊቀይር የሚችል አመጽ ሊያስነሱ እንደሚችሉ ተነበየ። እስክንድር ነጋ በያዝነው ሳምንት አርብ እለት ባወጣው ጽሁፍ ላይ፡ http://ethiomedia.com/above/2286.html በኢትዮጵያ ታሪክ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ባሳለፈው ስልሳ አመት እድሜው፤ በተፈራረቁበት ሶስቱ መንግስታት አስተዳደር ውስጥ የህብረተሰቡን ብሶት ይዞ በመነሳትና ለለውጥ በመታገል የነበራቸውን ሚና አብራርቶ፡ በዚህ በያዝነው የፈረንጆች አመት መጀመሪያ ጀምሮ በግብጽና በተቀሩት የአረብ አገራት እንደታየው፡ በኢትዮጵያም ተመሳሳይ ጥያቄ ሊያስነሱ ይችላሉ የሚል ጠንካራ እምነት እንዳለውና ምልክቶችም እየታዩ እንደሆነ ተናግሯል።