የቴሌ ኮሙኒኬሽን ሰራተኞች ሮሮ መልስ አላገኘም!

ስምንት ሺህ የሚደርሱ ሰራተኞች ተባረዋል!  

Ethiopia Zare (ረቡዕ የካቲት 23 ቀን 2003 ዓ.ም. March 2, 2011)የኢትዮጵያ ቴሌ ኮሞኒኬሽን አስተዳደር ፈርሶ በፈረንሳዩ ፍራንስ ቴልኮም ቁጥጥር ስር እንዲገባ ከተደረገ ጀምሮ ስምንት ሺህ  የሚደርሱ የቴሌ ሰራተኞች ከተባረሩ በኋላ የሚያሰሙት ሮሮ ተቀባይነት እንዳላገኘ ምንጮች ገለጹ።