በየመን ዩኤንኤችሲአር ያስገነጥላል፤ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያጨበጭባል

አምላክሥራ ግሩም

ለአንዳንድ ጉዳይ ወደ UNHCR ቢሮ ጎራ ስል ያለው አስቸጋሪ ሁኔታ የቢሮው ብልሹ አሠራር ያናድደናል – ለኢትዮጵያዊያን። ሰሞኑን እንኳ የስደተኛነት ማረጋገጫ ማንዴቴ ላይ ስሜ ሲጻፍ የቃላት ግድፈት አስተካክሉልኝ ብዬ አንድ የዘለሉዋትን ፊደል ለማስተካከል 10 ቀን ነው ያመላለሱኝ። ሙሉ ስሜን ቢሆን ስንት ወር ያመላልሱኝ ይሆን? ይህ ታዲያ ለኢትዮጵያዊያን ነው። ኢራቂ ከሆኑ መስተንግዶው ፈጣን ነው።