ቀዳሚተ ሰንበት ከዳዊት ከበደ ጋር – (ከሲያትል)

ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደን በዝና አውቀነው ቆይተን ነበር። ወደዚህች ምድር በነጻ ፈቃዳችን እንኖር ዘንድ የላከን እግዚያብሔር  ፈቅዶ ይሄው በአሲምባ ሬስቶራንት ተገናኘን። አሲምባ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ የአንድ ትልቅ ተራራ ስም ነው። በዚህ ተራራ ስር ሀገራቸውን ነጻ ለምውጣት ሲሉ የቀደሙ ወንድሞችና እህቶች የመሸጉበት ታሪካዊ ስፍራ እንደሆነ ሰምተናል። ይህ ታሪካዊ አምባ ተረስቶ አልቀረም ይሄው በፈረንጆቹ ሀገር የአንድ ግሩም ሬስቶራንት መጠሪያ ሆኗል። በዚህ ሬስቶራንት ውስጥ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደን አግኝተን በብዙ ጥያቄ ጠየቅነው። ከእሱም ጋር በላን ጠጣን ደስም አለን። ዳዊት ከበደ መለስ ዜናዊ ተወልዶ ካደገበት አደዋ ከተማ ነው የተወለደው።፡ አደዋ እንደመለስ ዜናዊ የመሰለውን ክፉ ሰው ብቻ ሳይሆን ዳዊት ከበደን የመሰለ ምርጥ ኢትዮጵያዊያንንም ትወልዳለች።