አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ ወደ ሩጫ መመለሱን አበሰረ
Ethiopia Zare (ሰኞ ኅዳር 6 ቀን 2003 ዓ.ም. November 15, 2010)፦ በረዥም ርቀት ውድድሮች ተደጋጋሚ የክብረ ወሰኖች ባለቤት የሆነው ኃይሌ ገብረሥላሴ በድጋሚ ወደ ሩጫ እንደሚመለስ በክብር እንግድነት የተገኘበት ነቀምት ከተማ ህዝብ ፊት በመቅረብ ይፋ አደረገ። ከኒው ዮርኩ ውድድር ነኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በቀጣይ ለሚደረገው የለንደኑ ውድድር ዝግጅቱን እንደሚቀጥልም አብስሯል።