የኢትዮጵያ ህዝብ … ከዚኽ ወዴት? (አያልሰው ደሴ)

የኢትዮጵያ ህዝብ፣ አገር-ወዳድና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች እና ኢህአዴግ፤ ከዚኽ ወዴት? ክፍል አስር

አያልሰው ደሴ (የግል አስተያየት)

በመሆኑም ምንም እንኳን በሁሉም ዘንድ በጎ-ፈቃድ ሊኖር ቢችልም፣ በአንድ በኩል ”ተባባሪ-አባል” በተባሉት (በአብዛኛው ፖለቲካዊ ባልሆኑ ስብስቦች) እና በኢሰዴአኃ፤ በሌላ በኩል ጉባዔውን ባዘጋጁትም ይሁን ኢሰዴአኃን በመሠረቱት ዋና ዋና በተባሉት ”አባላት” እና በኢሰዴአኃ (በአመራሩ) መኻል አለመጣጣሞችና ቅራኔዎች ብቅ ብቅ ማለት ሲጀምሩ ጊዜ አልወሰዱም።