የወያኔ አለንጋ እጅ ባሜሪካ
ይነጋል በላቸው
በ”ሠላም ለሁላችሁም!” ጀመርኩ ይህችን አጭር አስተያየት። የአቶ ዘውገ ፋንታን ሐተታ (በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌደሬሽን ስለ ዳኛ ብርቱካን ሚደቅሣ የክብር እንግዳነት ምርጫ የወሰደው ፖለቲካዊ አቋም) አነበብኩ። ሀገራችን የገጠማትን ዘርፈ ብዙ ችግር እያሰላሰልኩም ብዙ ተከዝኩ። የወያኔም እጅ ምን ያህል ረዥም እንደሆነ ታሰበኝ። ለነገሩ በብሂሉ ”አለንጋ ጣት” ነበር የሚባለው፤ ግን ነገርን እንዳደረጉት ነውና ”አለንጋ እጅ” አልኩና ተነሳሁ። ዳሩ ዛሬ ዛሬ ምን ባለበት ቆሞ ያለ ነገር አለና ልጨነቅ? ሁሉም ነገር ሊያውም በአሉታዊ መልኩ እየተለወጠ አይደል ያለ?