የከዘራው ትንቢት አልተፈፀመም እንዴ?
|
ይሄይስ አዕምሮ ትናንት ማታ የድረ ገጽ ዜናዎችን ሳነብ ያየሁት አስገራሚ ዜና በሌላ ጉዳይ ላይ ልጽፍ ተነሳስቼ የነበርኩትን ሰውዬ ወዲያውኑ አስለወጠኝ። ብቻየን በሳቅ ስንከረከር የራሴው የሳቅ ማሚቶ እንደገና እያሳቀኝ በቶሎ ላቆም አልቻልኩም – አስመሸኝ። የወያኔ ገልቱ ሥርዓት እንዴቱን ያህል የወዳጆቹን ብቻ ሳይሆን የጠላቶቹን ጭምር አንጀት በሚበላ አሳዛኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ስገነዘብ እኔ ራሴም ሆዴን ባር ባር አለው፣ ክፉኛ ተንቦጫቦጨለት፣ ሲያልቅ አያምር አሉ። የምሬን ነው። |