ብአዴን ለአማራው የመጣለት ወይስ የመጣበት
ቻሌ ተሾመ [email protected]
የአማራውን ክልል በመምራት ላይ የሚገኘው ብአዴን የተባለ የህወሓት ጥላ ድርጅት የተመሠረተበትን 30ኛ ዓመት በተመለከተ በዋሽንግተን ዲሲ በሞቀበት የሚዘፍኑ ሚዲያዎች ማስተጋባትን ይዘዋል። በተለይ በዚሁ ድርጅት ቀድሞ ታጋይ የነበርን የሚሉ የትግል ውሉና ጉዞው የጠፋባቸው ተጋባዦች የሰጡትን አስተያየት በተመለከተ አቶ ተድላ አስፋው ”Ethiopian Movement Vs Amahara national” በሚለው የእንግሊዝኛ መጣጥፋቸው በመዳሰስ ከኢትዮጵያዊ ስም ወደ ክልላዊ ስያሜ የተቀየረበትን ምክንያት በትክክል አስቀምጠውታል ብዬ አስባለሁ።