መድረኩ ሥር ነቀል ለውጥ ያስፈልገዋል

ግርማ ካሣ ([email protected])

ከጥቂት ሣምንታት በፊት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ አምስት ገጾች የያዘ መግለጫ አውጥቷል። በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አደገኛ ሁኔታ ላይ እየወደቀ እንደሆነ የገለጸው መድረክ፣ ኢትዮጵያ ወደ አንድ ግለሰብ አምባገነንነት እያመራች እንደሆነም በመግለጫው ያትታል።