”ወ/ሪት ብርቱካን ፖለቲከኛ እንጂ፣ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ አይደለችም”

ጽዮን ግርማ (የአዲስ አድማስ ጋዜጣ አዘጋጅ)

W/t Birtukanየአዲስ አድማስ ጋዜጣ አዘጋጅ የሆነችው ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ከእስር በተፈታችበት ዕለት ከቃሊቲ እስር ቤት ጀምሮ ፈረንሣይ በሚገኘው መኖሪያ ቤትዋ ድረስ የነበረውን ትዕይነት በዚህ ሪፖርቷ ታስቃኘናለች። የአንድነት አመራሮች (እነ ኢ/ር ግዛቸው) እንዲሁም የመርኅ ይከበር አባላት (እነ ፕ/ር መስፍን) በወ/ት ብርቱካን ቤት መገናኘትን፣ የፖለቲከኞቹን አስተያየት፣ የህዝቡንና የአካባቢውን ሰዎች አስተያየት ታ1ስነብበናለች። ወ/ት ብርቱካን ለጠ/ሚ መለስ ዜናዊ የፃፈችውን ደብዳቤ፣ የመንግሥት መገናኛ ብዙኀኑን ዘገባ፣ በተለይም በሰነዱ አንደምታ ላይ እና በ”ይቅርታው” ጉዳይ ላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፍልስፍና እና የኢንስቲትዩት ኦፍ ሂዩማን ራይት መምህር የሆኑት ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋን አናግራለች። ዶ/ር ዳኛቸው ሰነዱን ከአራት ነጥቦች አንጻር በመመዘን ሰፋ ያለ ትንታኔ ሰጥተዋል። ይህንን ሰፋ ያለ ሪፖርታዥ ታነቡ ዘንድ እንጋብዛለን! … መልካም ንባብ!