ስለወ/ት ብርቱካን ጠ/ሚ መለስ የማይደፍሩት ሐቅ

PM Meles Zenawiሠላማዊት

ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በአሜሪካው ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው ስለወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ሲጠየቁ በየመድረኩ ከሚለዋወጡት ምላሽ አንዱን መለሱ። ”ይቅርታ አልጠየኩም የሚል ሰው በሕጋችን መሠረት ይቅርታው ተነስቶ ውሳኔው ተፈፃሚ ይሆናል አሉ” (ቃል በቃል ስለመጥቀሴ ርግጠኛ አይደለሁም)። የትኛው ሕግ ይህን እንደሚል ግን አንቀጽ ጠቅሰው ማስረዳት አይችሉም። እንዲህ የሚል ድንጋጌ የያዘ አዋጅም ሆነ ደንብ የለም።