የኢትዮጵያ ህዝብ፣ አገር ወዳድና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች እና ኢህአዴግ ከዚኽ ወዴት? (አያልሰው ደሴ)
ከአያልሰው ደሴ (የግል አስተያየት)
ክፍል ሦስት (ከክፍል ሁለት የቀጠለ)
ሐ) አገር ወዳድና ህዝባዊ (ዴሞክራሲያዊ) ኃይሎች፤
ከፍ ሲል በ’ለ’ ስር ለማሳየት እንደተሞከረው ለሀገራችንና ለህዝቧ አዎንታዊ ለውጥን ለማስገኘት በልዩ ልዩ መልክ የሚጋገለውና በጥቅሉ ”ተቃዋሚ ክፍል” የተባለው ወገን ሥልጣን ላይ ካለው ገዥ ክፍል ከኢህአዴግ ጋር የሚኖረውን አንፃራዊ አሰላለፍ በተገቢ መመርመር ያስፈልጋል።