የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስታር አሊያንስ አባል ሆነ

Mr. Jaan AlbrechtAto Girma WakeEthiopia Zare (ሐሙስ መስከረም 20 ቀን 2003 ዓ.ም. September 30, 2010)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ”ስታር አሊያንስ” የተሰኘውን ዓለም አቀፍ የአየር መንገዶች ሕብረት በሚቀጥሉት 12 ወራት ለመቀላቀል ረቡዕ መስከረም 19 ቀን 2003 ዓ.ም. ተፈራረመ። አየር መንገዱ ከግብፅ እና ከደቡብ አፍሪካ ቀጥሎ ሕብረቱን ሲቀላቀል ሦስተኛው የአፍሪካ አየር መንገድ ይሆናል።