ኢራናውያን እገዳውን ጥሰው ሰልፍ ወጡ

በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢራናውያን ትናት ሰኞ (08. 06.2003 ዓ.ም.) አደባባይ መውጣታቸው ተዘገበ። ሰልፈኞቹ የኢራን መንግስትን ሲቃወሙ በአንፃሩ ለግብፅና ቱኒዚያ የዲሞክራሲ ንቅናቄ ድጋፋቸውን አሳይተውበታል። የኢራን የፀጥታ ሀይላት በሰልፈኛው ላይ ምህረት አልባ ርምጃ መውሰዳቸውም ተጠቅሷል።

በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢራናውያን በግብፅና ቱኒዚያ የተከናወኑ የዲሞክራሲ ንቅናቄዎችን በመደገፍ ትናት ሰኞ ሰልፍ መውጣታቸው ተዘገበ። ከሰልፈኞቹ መካከል የሞተ ሰው እንዳለ በርካቶቹም ጭንቅላታቸውን ንዝረት በሚፈጥር ዱላ እንደተደበደቡ ተጠቅሷል። በዶቼ ቬሌ የፋርስ ክፍል ባልደረባ የሆነችው ኢራናዊቷ ሻብናም ኑሪያን ሰልፉን የተመለከተ ዘገባ አላት። ማንተጋፍቶት ስለሺ እንደሚከተለው አጠናቅሮታል።

ያድምጡ