በቴፒ ዩኒቨርሲቲ የኦሮሞ ተማሪዎች ላይ ጥቃት ደረሰ
የአፍሪቃ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ሊግ በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የመንግሥት ወታደሮች በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ በወሰዷቸው የኃይል እርምጃዎች በርካቶች ተጐድተዋል አለ። በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የትግራይ ተማሪዎች ከፖለቲካና ጐሣ ጋር የተያያዙ ጥቃቶችን በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ ማድረሳቸውን አስታወቀ።
ከታሠሩት ውስጥ አራቱ ወደ አዲስ አበባ ተይዘው መወሰዳቸውንም ድርጅቱ አስታውቆ በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ ያነጣጠረው ጥቃት እንዲያበቃ የታሠሩት ባስቸኳይ እንዲፈቱና የተቋረጠው ትምህርት እንዲቀጥል ያደርግ ዘንድ ለመንግሥት ተማጽኖ አቅርቧል።
ይህን የሰኞውን አስቸኳይ የተማጽኖ ጥሪ ያወጣው ዋና ጽሕፈት ቤቱን በቶሮንቶ ካናዳ ያደረገው የአፍሪቃ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ሊግ የተባለው የመብቶች ተሟጋች ድርጅት ሲሆን ኃላፊው አቶ ጋሩማ በቀለ ዋቀሣ ይባላሉ።
ድርጅቱ በተለይ በተለያዩ ጊዜአት ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በፖሊስ ተይዘው ወደ አዲስ አበባ ከተወሰዱ በኋላ የደረሱበት ጠፍቷል የተባሉትን የአራት ተማሪዎች ስም ዝርዝር በመግለጫው ያወጣ ሲሆን፥ እነርሡም፥ ግርማ ቱሩና እና ደቻሣ ዊርቱ ሞሲሣ ከሓሮማያ ዩኒቨርሲቲ፥ ጋዲሣ ረጋሣ ከሐዋሳ፥ ፈይሣ ፉፋ ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ መሆናቸውን አስታውቋል። የተያዙባቸውን ቀናትም አስቀምጧል።
ከዚህም በተጨማሪ ከብጥብጡ በኋላ የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የኦሮሞ ተማሪዎች የመታወቂያ ካርዶቻቸውን እንደተነጠቁና ለጊዜውም ቢሆን በሁኔታው የተደናገጡ ከትግራይ ተወላጆች በስተቀር የቀሩት ተማሪዎች በሙሉ ካምፓሱን ለቅቀው ለመሸሽ መገደዳቸውን ካካባቢው ዜና ተላላኪዎቹ መረዳቱንም ድርጅቱ ገልጿል።
በሌላ በኩል ደግሞ፥ ያካባቢው ባለሥልጣናት ከትራንስፖርት አቅራቢ ድርጅቶች ጋር በመነጋገር ወደየዘመዶቻቸው መመለስ የሚፈለጉ ተማሪዎች በየትኛውም አቅጣጫ እንዳይወጡ መከልከላቸውንም ድርጅቱ ጨምሮ አስረድቷል።
የድርጅቱ ዜና አቅራቢዎች እንደገለጹለት በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲው ግጭት ጉዳት የደረሰባቸው አብዛኞቹ ተማሪዎች ወደ ጂማ ሆስፒታል ተወስደው የህክምና እርዳታ አግኝተዋል።
የአፍሪቃ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ሊግ በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ነው ያለው የጥቃት ዘመቻ ባስቸኳይ ይቆም ዘንድ ተማጽኖውን ለአትዮጵያ መንግሥት ከማቅረቡም በላይ ተቆርቋሪዎች ጉዳዩን በኢትዮጵያ ለሚገኙ የኤምባሲ ተጠሪዎች በሙሉ እንዲያሳውቁም ጠይቋል።
መግለጫውን ጄኔቭ ለሚገኘው የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኰሚሽን፥ የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኰሚሽነር-ዩኤንኤችሲአር፥ ባንጁል-ጋምቢያ ላለው የአፍሪቃ የሰብዓዊ መብቶች ኰሚሽን፥ ለዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፥ ለአምነስቲ ኢንተርናሽናልና ለሒዩመን ራይትስ ዋች በግልባጭ አስታውቋል።
በዚህ መግለጫ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ያለውን ምላሽ ለማግኘት ወደ አካባቢው ባለሥልጣናት ቢሮ እንዲሁም አዲስ አበባ ወደ ፌዴራሉ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ያደረግናቸው የስልክ ጥሪዎች ለዛሬ ምላሽ አላገኙም። ጥረታችን ነገም የአፍሪቃ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ሊግ በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የመንግሥቱ ወታደሮች በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ በወሰዷቸው የኃይል እርምጃዎች በርካቶች ተጐድተዋል አለ።ይቀጥላል።
I wonder why weyane is complaining about OLF while they are abusing the Oromo students in their home town as the same time Weyane is the one show Ethnicity to everyone in Ethiopia. And hopefully the
students from Tigray should understand and stand for their fellow students if not there will be a pay back.
ANY BODY WHO LOVES ETHIOPIA SHOULD SAY SOMETHING AGAINST THIS KIND OF RACIST ATTACK ON OROMO PEOPLE ALL THE TIME!!!..THEN WE FEEL WE ARE AND WE ARE ETHIOPIANS!!
TPLF has gone to fighting with Derg to free Ethiopians from official supressing Derg Regime. The International community has helped a lot achieving those objectives. But the support was to free Ethiopians not for TPLF himself. However,when TPLF came to power, supression, harrasment, frustration, killing, arresting, corruption /It is roumered that the officially of TPLF dollar reserve outside Ethiopia reached an amount which can establish the so called Hidase/ Millenium Dam on Abay. I personally advise the officials donate their Dollar first and we will raise fund thereafter/, controlling of economy by TPLF, has turned its face to a systematic one. Every body should consider that only TPLF officials and their key allies control and rule the country by their rule of the jungle. Infact, they used to be military persons. Military person always think of Feast Arms. Nothing Else. They Use it everywhere even in the economy.
The fact that the oromo students suffer from harasement and prison is that their continued inqury about freedom and power balance.
Instead of good reply, which is sharing of power legitimately and equitably, oh I forget, the regim itself was not legitimate after 1997 EC Election fraud. …..next time
why we always fighting each other?why don’t we unite our selfs to fight our enemy ,poverty,? why don’t we stand together rather than fighting for our little differences we got? we are Ethiopians we love our country, so lets unite ourself as one nation for the future.