የጀርመን ሠራዊትና የአፍጋኒስታን ተልዕኮው

የጀርመን መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ባለፈው ቅዳሜ ሳይታሰብ በአፍጋኒስታን የሚገኙትን የሀገራቸውን ወታደሮች ጎበኙ። ጀርመናውያኑ ወታደሮች በጦርነት ላይ እንደሚገኙ ሜርክል በዚሁ ጉብኝታቸው ወቅት ባሰሙት ንግግራቸው በግልጽ አስታውቀዋል።